dagnaw manew

€9.99
In stock
SKU
dagnaw manew

 

ጸሐፊዋ ታደለች ኃ/ሚካኤል ለትምህርት በቆዩበት ስዊዘርላንድ ፣ ዲሞክራሲ ፣ ፍትህና እኩልነት በአገር ውስጥ እንዲሰፍን ከሚታገሉት የኢሕአፓ እንቅስቃሴ መሪዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ፈጥረዋል። ይህም ወዳላሰቡት የፖለቲካ አለም አስገብቷቸዋል። በአውሮፓ ስዊዘርላንድና በአገር ውስጥ ተሳትፏቸውን አጎልብተው ፣ በመርሃቤቴና በመንዝ የትጥቅ ትግል እስከመመስረት ተጉዘዋል። የኢሕአፓ መሥራች የሆነው ባለቤታቸውና የሦስት ሴት ልጆቻቸው አባት ብርሃነመስቀል ረዳን ለሞት የዳረገው ምክንያት ሆኗል። ከእስር ከተፈቱም በኋላ የመጀመሪያዋ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ለ11 ዓመታት እንዲሁም በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት በኮትዲቯር እና በፈረንሳይ ለ8 ዓመታት አገልግለዋል።

“በድብቅ ይካሄድ የነበረው የብርሃነ መስቀልና ታደለች የፍቅር ሕይወት ሦስት ልጆችን አፍርቷል። እነሆ አሁን ደግሞ ልጃቸው በዚህ መጽሐፍ መልክ ተከስቷል። ዘግይቶ የመጣ ቢሆንም የፍቅርና የትግል ሕይወታችውን ሙሉ ስዕል ለማግኘት በእጅጉ ይረዳል። ስለሆነም በዘመኑ ከተጻፉ ትውስቶች መካከል ቁንጮ ስፍራ ሊይዝ የሚገባው ትርክት እንደሚሆን አያጠራጥርም።”

ባሕሩ ዘውዴ (የታሪክ ፕሮፌሰር አ.ሚሬተስ)

“ለኢትዮጵያ አዲሱ ትውልድ እና ስለዓለም ሕዝባዊ ትግሎች ጥናት ለሚያደርጉ ተማሪዎች እጅግ ጠቃሚ ንባብ ነው። እህታችን ታደለች የሰጠችው ሀቀኛ ፣ ሚዛናዊ እና ልባዊ ምስክርነት ለሁላችንም ባለውለታ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው።”

እንድርያስ እሸቴ (የፍልስፍና ፕሮፌሰር)

ብርሃነ መሰቀል በዳይ ወይንስ ተበዳይ? የዛን ትውልድ ውስብስብ ታሪክ አንድ ገጽታ ይዛልን አምባሳደር ታደለች ቀርባለች። በዳኛው ማነው? የዛን ትውልድ መስዋዕትነት በተለመደ ግልጽነቷና ሰብዓዊነት በተላበሰ አቀራረብ በጥሩ ቋንቋ ገልጸዋለች።”

ልኡል በዕደማርያም መኮንን

“የታዲ ውብ የፍቅርና ሰፊ የፖለቲካ ትርክት ከትውልድ እየተሻገረ በአላማ መጽናት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ሊያስከፍል መቻሉን ያሳያል ፣ ትምህርት ሲጪ እንደሚሆንም ተስፋ አደርጋለሁ።”

ወ/ሮ እንጉዳይ በቀለ (በባህር ዛፎች ጥላ ስር መጽሐፍ ጸሐፊ)

“በንቃት ለተሳተፈችበት ትግል፣ በጽናት ለተቀበለችው የመከራ ዘመን ፣ ለእምነትና ለፍቅር ለከፈለችው መስዋዕትነት የሚመጥን የታሪክም የስነ ጽሁፍም ሰነድ”

ማስረሻ ፈጠነ (የእጽዋት ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር እኢሚሬተስ)

 

  BOOK DETAIL

Author   Tadelech H/mikael

 Year  2021

price  295 birr

Type  Biography